HOME
ABOUT US
SERVICES
NEWS
CONTACT US
Save today for better future
About
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ዋና ዋና አላማወች
አባላትና ብሎም ኀብረተሰቡ የሚያገኙት ገቢ በስርዓት እንዲጠቀሙበት ትምህርት መስጠት፣
አባላት በማኀበራቸው ገንዘብ እንዲቆጥቡ በማድረግ ኑሮአቸውን ማሻሻል፣
ለአባላት ፈጣንና ምቹ በሆነ መንገድ በተገቢው ወለድ የብድር አገልግሎት በመስጠት ኀብረተሰቡን ኋላቀር ከሆኑና ለብዝበዛ ከሚያጋልጡ አራጣና ሌሎች የብድር ልምዶች ማላቀቅ፣
ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም በመፍጠር ሌሎች ባንክ ነክ አገልግሎት መስጠት፣
በግለሰቦች እጅ ተበታትኖ የሚገኘውና በሥራ ላይ ያልዋለውን ገንዘብ በቁጠባ በማሰባሰብ የአገሪቱን ማዕከላዊ የገንዘብ ክምችት ማዳበር፣
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ተግባር
የመመዝገቢያ ክፍያ፣ የዕጣ ክፍያ፣ መደበኛ ቁጠባ፣ መደበኛ ያልሆነ ቁጠባ፣ የአገልግሎት ክፍያዎችንና ሌሎች ገቢዎችን ከአባላት መሰብሰብ፣
በየጊዜው እንደአስፈላጊነቱ ዕጣ አዘጋጅቶ መሸጥ፣
በብድር መመሪያው መሠረት የብድር አገልግሎት መስጠት፣ ተበዳሪ አባላት ገንዘባቸውን በአግባቡ መጠቀም ይችሉ ዘንድ ተገቢውን ምክር፣ዕገዛ፣ ክትትል፣ ትምህርት መስጠት፣ ለብድር የተሰጠው ገንዘብ በወቅቱ ከነወለዱ እንዲመለስ አስፈላጊውን መፈጸም፣
በቁጠባ ሂሳብ ለተቀመጠ ገንዘብ ተገቢውን ወለድ ማሰብ፣
ለማህበሩ ጥቅም በሚያስገኝ ቦታ ገንዘብ ማስቀመጥ፣
መደበኛ ያልሆነ ቁጠባውን ግለሰቦች ወጪ ለማድረግ በጠየቁ ጊዜ ማስተናገድ፣
ተከታታይ ትምህርት፣ መረጃና ሥልጠና ለአባላት፣ ለአመራር አካላት፣ ለቅጥር ሰራተኞች እና አባል ለሚሆኑ ግለሰቦች መሰጠት፣
ለስራው የሚያስፈልጉትን ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ማፍራትና ማስተዳደር፣
የኀብረት ሥራ ማኀበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን ወይም ፌደሬሽን አባል ለመሆን ዕጣዎችን መግዛት ቁጠባዎችን መቆጠብ፣
ማኅበሩ በተቋቋመበት አካባቢ ለሚኖረው ኅብረተሰብ ለውጥ የሚያመጡ/ጥቅም የሚያስገኙ የተለያዩ ዓይነት ብድሮችን ተረክቦ ማሰተዳደር፣
ለአባላት የተለያዩ አነስተኛ የመድን /Micro Insurance/ሽፋን አገልገሎት መስጠት፣
የኀብረት ሥራ ማኀበራት እሴቶች
ራስን በራስ መርዳት፣
የግል ኃላፊነት መወጣት፣
ዲሞክራሲን ማስፋፋት፣
እኩልነት፣
ፍትሐዊነት፣
አንድነትና የጋራ መደጋገፍ ናቸው፡፡
የኀብረት ሥራ ማኀበራት መርሆዎች
አባልነት በፍቃደኝነትና በፍላጐት ላይ የተመሠረተና ለሁሉም ክፍት የሆነ፣
ዲሞክራሲያዊ አሠራርና አመራር፣
የአባላት ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ፣
ነፃና ራስን በራስ ማስተዳደር፣
ተከታታይ ትምህርት፣ ስልጠናና መረጃ መስጠት፣
ከሌሎች አቻ ኀብረት ሥራ ማኀበራት ጋር ኀብረት መፍጠር፣፡
ለአካባቢ ዘላቂ ልማት ጥረት ማድረግ፣
የብድር እና ቁጠባ ማህበራት ለአባላት በተመጣጣኝ ወለድ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ፣ ፈጣን ምቹና በቅርብ የሚገኝ የፋይናንስ ስርአት ለመዘርጋት፣ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ስራ አጥነትን ለመቀነስ፣ ማእከላዊ የገንዘብ ክምችት ለመፍጠር፣ የብድር አጠቃቀም ልምድን ለማዳበር የሚረዱ ተቋማት ናቸው።
News
ለሁሉም አባላት በሙሉ
ከዚህ በፊት መስከረም 26 ቀን በተደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጸድቆ ስራ ላይ የነበረውን መመስረቻ ጽሁፍና መተዳዳሪያ ደንብን በማዋሃድ አንድ መመስረቻ ጽሁፍ ሰነድ ማድረግ አስፈላጊ ሁኖ ማገኘቱ ይታወቃል። ስለሆነም ሚያዚያ 06 ቀን 2017 ዓም ከቀኑ 8 ሰዓት በተቋሙ አዳራሽ ለስብሰባ እንድትገኙ ስንል እናሳስባለን።
በየቀኑ የተቀመጡ አነስተኛ ቁጠባዎች በመጨረሻ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችን ይጨምራሉ።
እንኳን አደረሳችሁ
ጉባኤው የኩባንያውን አመታዊ አፈፃፀም፣ የትርፍ ክፍፍል፣ የደረሰበትን የካፒታል መጠን እንዲሁም አዳዲስ አባላትን ያሳወቀ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት አመት ከታክስ በፊት 20 ሚሊየን ብር ትርፍ መገኘቱም ታውቋል። በአሁኑ ሰአት ኩባንያችን ከአሃት ኩባንያዎች ጋር በመሆን 16ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓሉን በማክበር ላይ እንደሚገኝ የሚታወስ ሲሆን ለሁሉም የኩባንያችን ባለአክሲዮኖች እንኳን አደረሳችሁ ማለት እንወዳለን።
Contact Us
Phone
+251953243744
Email
simegnishmulat1@gmail.com
Telegram
Telegram link